ሆስፒታሉ የደም ልገሳ መርሀ-ግብር አከናወነ

አዲስአበባ – የካቲት 28 – 2016 (ቅ.ጴ.ስ.ሆ)

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዘንድሮ በጤናው ዘርፍ “የሴቶችን አቅም በማጎልበት፤ የጤና ልማቱን እናፋጥን” በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን ዓለምዓቀፍ የሴቶች ቀን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ የደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባበር የደም ልገሳ መርሀ-ግብር አከናውኗል።

የደም ልገሳ መርሀ-ግብሩ የተከናወነው በዓለምዓቀፍ ደረጃ ለ114’ኛ ፤ በሀገራችን ደግሞ ለ48’ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለምዓቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 😎 በማስመልከት ነው።

በወሊድ ምክንያት ደም ለሚያስፈልጋቸው ወላዶች እና በካንሰር ህክምና ላይ ለሚገኙ ህፃናት ደም ተደራሽ ለማድረግ የሆስፒታሉ ሰራተኞች እና አስታማሚዎች “ዓለምዓቀፍ የሴቶች ቀንን ደም በመለገስ አብረን እናክብር” በማለት በሆስፒታሉ ውስጥ በአብሮነት የደም ልገሳ ሲያደርጉ ውለዋል።

ሆስፒታሉ የአሁኑንም ጨምሮ ከዚህ ቀደምም ከኢትዮጵያ የደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባበር በተለያዩ ጊዜያት በህፃናት ፣ ሴቶችና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት በኩል የደም ልገሳ መርሀ-ግብሮች በማዘጋጀት እና ከበጎ ፍቃደኛ ለጋሾች ደም እንዲሰበሰብ በማድረግ የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

_____________

“መኖራችን ለእርስዎ ነው!”

“OUR EXISTENCE IS FOR YOU!”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top