አዲስአበባ – የካቲት 17- 2016 (ቅ.ጴ.ስ.ሆ)

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተገኝተው የMEMIS ፕሮጀክት የስራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የሚኒስትሯ ጉብኝት አላማ በዋናነት በUSAID የሚደገፈውን የMEMIS ፕሮጀክት አፈጻጸምን በመገምገም በቀጣይነት መንግስት ስራውን ተረክቦ እንዲያስቀጥለው ለማስቻልና ለመገምገም ነው።

ሚኒስትሯ በቆይታቸው የዲጂታል ሄልዝ ኢኖቬሽን ማዕከልንና የሆስፒታሉ የባዮ ሜዲካል ክፍል የጎበኙ ሲሆን በMEMIS ፕሮጀክት ዙሪያ ላይ ከUSAID ዲጂታል ሄልዝ የዲጂታላይዜሽን ዳይሬክተር በአቶ ብሩህ ተስፋ አበረ በኩል ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

በኢኖቬሽን ማዕከሉ የዕውቀት ሽግግር እንዲኖርና በዚህ ሲስተም ውስጥ የሚሳተፉ ጤና ተቋማት ቁጥር እንዲጨምር አፈጻጸሙ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ሚኒስትሯ ያስገነዘቡ ሲሆን የሆስፒታሉ ባዮ ሜዲካል ትልቅ ወርክሾፕ ኖሮት እንደማሰልጠኛ ማዕከል እንዲያገለግል ለሆስፒታሉ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደረግ ገልጸዋል።

MEMIS (Medical Equipment Management Information System) በሀገሪቱ በየጤና ተቋማቱ የሚገኙ የህክምና መሳሪያዎች ሲበላሹ ጥገና እንዲያገኙ ለማድረግ እንዲሁም የህክምና መሳሪያዎቹ ያሉበትን ሁኔታ መረጃ መዝግቦ ለመያዝ የሚያስችል የመረጃ አያያዝ ስርዓት ሲሆን በዩኤስ አይድ ድጋፍ በሆስፒታሉ እየተሰራ ያለ ፕሮጀክት ነው።

_________________

“መኖራችን ለእርስዎ ነው!”

“OUR EXISTENCE IS FOR YOU!”

Scroll to Top