የ2016 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አመራሮች በሆስፒታሉ በህክምና ላይ ከሚገኙ ህሙማንና ሰራተኞች ጋር በደስታ አክብረው ውለዋል።
በተለያዩ የህክምና ክፍሎች ለሚገኙ ህሙማን የእንኳን አደረሳችሁ ፖስት ካርድና አበባ በመስጠትና 2016 ዓ.ም ጤናቸው ተመልሶ መልካም ዘመን እንዲሆንላቸው በመመኘት አብሮነታቸውን አሳይተዋል። እንዲሁም በሆስፒታሉ በዛሬው ዕለት ለወለዱና ህክምናቸውን እየተከታተሉ ለሚገኙ ወላድ እናቶችም የዳይፐርና ሞዴስ ስጦታ በመስጠት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም በዓልን ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው በስራ ላይ እያሳለፉ ከሚገኙ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ጋር በጋራ ማዕድ በመካፈል በዓሉን በደስታ አሳልፈዋል።
የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር መታሰቢያ መስፍን በዓላትን በአብሮነት ማሳለፍ በሰራተኛው መካከል የእርስ በእርስ ቅርርብን እንደሚያጠናክር ገልጸው በ2016 ዓ.ም ሆስፒታሉን የበለጠ ውጤታማና ስኬታማ ለማድረግ መላው ሰራተኞች ከመቼውም ጊዜ በላይ እንዲጥሩ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ 2016 ዓ.ም መልካም የስራና የስኬት ዘመን እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል።
መልካም አዲስ ዓመት!